Showing posts with label News. Show all posts
Showing posts with label News. Show all posts

ለ10 ሺህ የጤና ባለሙያዎች የመኖሪያ ቤት ሊገነባ ነው።

ለ10 ሺህ የጤና ባለሙያዎች የመኖሪያ ቤት ሊገነባ ነው።


ለ10 ሺህ የጤና ባለሙያዎች የመኖሪያ ቤቶችን ገንብቶ ማስረከብ የሚያስችል ቅድመ ሁኔታዎችን እያደረገ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።



ሚኒስቴሩ መኖሪያ ቤቶችን ገንብቶ ለማስረከብ በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ከ'ጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ' ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጋር ውይይት አድርጓል።


ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር አየለ ተሾመ እንዳሉት፤ በአገሪቱ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ረዥም ዓመት የቆየ ነው።


የተዘጋጀው የቤት ግንባታ ፕሮግራም የጤና ባለሙያዎችን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት የሚረዳና የባለሙያዎቹን የረዥም ጊዜ ጥያቄ የሚመልስ ነው ሲሉ አስረድተዋል።


ፕሮግራሙ የጤና ባለሙያዎች በአነስተኛ ወርሃዊ የቁጠባ ሒሳብ የቤት ባለቤት የሚሆኑበትን ለመፍጠር የሚያስችል እንደሆነም ገልጸዋል።


የ'ጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ' ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ዋና ሥራ አስኪያጅ አልማው ጋሪ በበኩላቸው፤ ግንባታው ተመጣጣኝ እና የዘመኑን የግንባታ ቴክኖሎጂ ታሳቢ ባደረገ መልኩ ይከናወናል ብለዋል።


በዚህም ድርጅቱ በአዲስ አበባ ከተማ ሊሰራ ካቀደው 100 ሺህ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ 10 ሺህ ቤቶችን ለጤና ሙያተኞች በአምስት ዓመት ገንብቶ ለማስረከብ እቅድ ይዟል።


እቅዱ እንደ አጠቃላይ በከተማዋ ያለውን የመኖሪያ ቤቶች ችግር በመቀነስ ረገድ ትልቅ እገዛ የሚያደርግ መሆኑንም ገልጸዋል።


 ይከታተሉን

የኢትዮጵያ ትምሕርት ሚኒስቴር በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ የሚፈጸመውን የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ስርቆት ለመከላከል ፈተናውን በታብሌት ለመስጠት ማቀዱን አስታውቋል።



         የኢትዮጵያ ትምሕርት ሚኒስቴር በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ የሚፈጸመውን የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ስርቆት ለመከላከል ፈተናውን በታብሌት ለመስጠት ማቀዱን አስታውቋል። የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ብርሃኑ ነጋ ትናንት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡበት የዘጠኝ ወራት የስራ አፈጻጸም ዘገባ ላይ ለዚሁ ተግባር የሚውሉ አንድ ሚሊዮን ታብሌቶችን ለመግዛት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። ከዚህ ሌላ በየትምህርት ቤቱ ፈተና ከመስጠት ይልቅ ተማሪዎች በየከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዲፈተኑ ለማድረግ አንደ አንድ አማራጭ መፍትሄ መታሰቡንም ተናግረዋል።









የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ

 

          Registration deadline: 8th April 2022 (+0 days left)


[ተመዛኞች ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መመሪያዎች በጥሞና ማንበብና ተግባራዊ ማድረግ ይኖርባቸዋል]

መመሪያ/Instruction/

  1. በዚህ ሲሰተም ላይ የመፈተኛ ጣቢያ(Exam Center) መምረጥ የምትችሉት ከየካቲት 30 እስከ መጋቢት 18/2014 ዓ.ም የተመዘገባችሁና ማረጋገጫ(Confirmation) የደረሳችሁ ተመዛኞች ብቻ ናቸሁ።
  2. የፈተና ጣቢያ ምርጫውን ለማካሄድ ተመዛኞች በምዝገባ ወቅት የተመዘገባችሁበትን ስም በትክክል ስፔሊንግ(Spelling) ማስገባት ይኖርባችኋል::
  3. የስም ስፔሊንግ(Spelling) አለመጣጣም ኖሮ ሲስተሙ ያስገቡትን ስም አልቀበል ካለ በቢጫ ሰንጠረዥ ከተዘረዘሩት የስም አማራጮች ላይ የስማችሁን ስፔሊንግ(Spelling) በመመልከት ሲስተሙ የመዘገበውን የስማችሁን ስፔሊንግ እንደገና በመፃፍ መግባት ትችላላችሁ::
  4. የመፈተኛ ጣቢያ ምርጫ አድርጋችሁ ስትጨርሱ የሚመጣውን ፎቶ የያዘ መለያ ካርድ(Identification Card) ኘሪንት(Print) ማድረግ ይኖርባችኋል::
  5. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0118275936/0118275337 ደውለው መረጃ መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን:

 

 

 


 

 

 

 

የኮሌራ ክትባት ዘመቻ በአማራ ክልል በመልካም ሁኔታ እየተካሄደ ነው

 

 


 

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በትላንትናው ዕለት ማለትም መጋቢት 21/2014 በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ደባርቅ ከተማ ያስጀመረው የኮሌራ በሽታ መከላከያ ክትባት ዘመቻ በተሳካ መልኩ እየተካሄደ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ክትባቱም እስከ መጋቢት 25/2014 የሚቀጥል ሲሆን ቤት ለቤት እና በተፈናቃዮች መጠለያ የሚሰጥ ይሆናል፡፡ ክትባቱ በዋነኛነት በቦታው የሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖችን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡

በክትባቱ ዘመቻ የማስጀመሪያ ንግግራቸው የአማራ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አቶ በላይ በዛብህ እንደተናገሩት በክልሉ 135000 ተፈናቃዮች የሚገኙ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 5000 የሚሆኑት በስደተኛ መጠለያ ካምፕ የሚገኙ ሲሆን ከዚህ በላይ ደግሞ ያሉት በሕብረተሰቡ ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ ናቸው፡፡ እንደ አቶ በላይ ገለጻ ቀደም ብሎ ክትባት ለሚሰጡት ባለሙያዎች ስልጠና የተሰጠ ሲሆን የክትባቱ ሂደትም በተሳካ መልኩ እንደሚካሄድ ገልጸዋል፡፡

አቶ ችሎት ተቀባ የደባርቅ ከተማ ምክትል ከንቲባ በበኩላቸው ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በመገንዘብ በተለይ በተፈናቃዮች መጠለያ ሊፈጠር የሚችለውን ወረርሽኝ ግምት ውስጥ በማስገባት የበሽታውን ክትባት በደባርቅ ማስጀመር በመቻሉ ለዚህም ከፍተኛ ጥረት ያደረጉትን በክልሉ ሕብረተሰብ ስም ማመስገን እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለው አባይነህ የክትባት ዘመቻውን ሲያስጀምሩ እንዳሉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዓላማ በሽታ ከመፈጠሩ በፊት ቀድሞ መከላከል እና ቅድሚያ ትኩረት የሚያስፈልጋቸውን አከባቢዎች በመለየት የሚያስፈልገውን የቀድሞ መከላከል ስራ ማካሄድ እንደመሆኑ አሁን መጪውን የክረምት ወራት ግምት ውስጥ በማስገባት የዚህ ክትባት ዘመቻ በዚህ ክልል እንዲካሄድ ተደርጓል በማለት የገለጹ ሲሆን በሽታውን መከላከል የሚቻል ሲሆን ዋናው የንጸሁህ ውሃ አቅርቦትን ማመቻቸት እንደመሆኑ ይህም እየተሰራበት መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በስተመጨረሻም ሁሉም የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም የዝግጅቱ ተሳታፊዎች በደባርቅ ከተማ ቁልጭ ሜዳ በመባል በሚታወቀው ቦታ የሚገኘውን የስደተኞች ጣቢያ የጎበኙ ሲሆን የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለው በመጠለያ ጣቢያው የሚገኘውን የጤና ጣቢያ፣ የስደተኞቹን መኖሪያ፣ የውሃ አቅርቦት ሁኔታ፣ ወዘተ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

 

Ethiopia: ሩሲያ ሁለተኛውን ዙር ጦርነት ጀመረችው | Russian Vs Ukraine war

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ትናንት ቅዳሜ በዶሃ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ባሰሙት ያልተጠበቀ የቪድዮ ንግግራቸው ነዳጅ አምራች አገሮችና ሌሎች አገሮች የሩሲያን የኃይል አቅርቦት የሚተካ ተጨማሪ የምርት እንዲያቀርቡ አሳስበዋል፡፡

እኤአ ከየካቲት 24 ጀምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍል ተማጽኗቸውን ሲያሰሙ የቆዩት ዘለንስኪ፣ በዶሃ ንግግራቸው፣ ሩሲያ በማሪዩፖል የምታደርሰውን ውድመት ሩሲያና ሶሪያ በሶሪያው ጦርነት በአሌፖ ላይ ካደረሱት ውድመት ጋር አመሳስለውታል፡፡

ዘለንስኪ በንግግራቸው፣ “ወደቦቻችንን እያወደሙ ነው፡፡ ከዩክሬን ምንም ነገር አይላክም ማለት በመላው ዓለም ለሚገኙ አገሮች ትልቅ አደጋ ነው” ብለዋል፡፡

ከዩክሬን የሚላከው ስንዴ በመከካለኛው ምስራቅ እንደ ግብጽ ባሉ አገሮች ላይ ከወዲሁ ከፍተኛ ችግር እያስከተለ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ዘለንስኪ በተለይ በዓለም ላይ የተፈጥሮ ጋዝ በማምረት ቀዳሚነትን የያዘቸው ኳታርን ጨምሮ አገሮች ምርታቸውን ከፍ በማድረግ የሩሲያን ተጽእኖ እንዲገቱ አሳሰባዋል፡፡

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ትናንት ቅዳሜ በዶሃ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ያልተጠበቀ የቪድዮ ንግግር አሰምተዋል፡፡ እኤአ መጋቢት 26 
 
 
KST amharic

KOSOBER-JOBS 💼💼💼

Kosober Jobs Your one-stop shop for finding and applying to jobs Kosober Jobs is a simple and easy-to-use career site that helps you find ...